21-30 July 2026

Bulletin

በጁላይ ሶስተኛዉ አስራ አንድ ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት ይኖራቸዋል ።