21-30 April 2026

Bulletin

በኤፕሪል የመጪዎቹ አሥር ቀናቶች ለበልግ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፣ ስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ገፅታ ይኖራቸዋል ፡፡