በፌብርዋሪ የሶስተኛው ስምንት ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በስምጥ ሸለቆ እና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ መካከለኛውና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይጨምራል፡፡ በተለይም በመጨረሻዎቹ ቀናቶች ላይ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ በመካከለኛው፣ የስምጥ ሸለቆ እና አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡