21-20 September 2025

Bulletin

በሚቀጥሉት የሴፕቴምበር ሶስተኛው አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም ከተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች መረዳት እንደተቻለው ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም በፀኃይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል ::