20-30 April 2025

Bulletin
Document

በኤፕሪል የመጪዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በምስራቅ፣ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በበልግ አብቃይ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡