11-20_September _2024

Bulletin

በመጪዎቹ የሴፕቴምበር ሁለተኛው አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በፀኃይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ (ካርታ 6)፡፡