በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ፣ በደቡም ምዕራብ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ ፡፡