11-20_August_2024

Bulletin

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን፤ በየጣልቃው የሚኖረው ፀሐይ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ ቁልል ደመና፣ በረዶ፣ ነጓድጓድ፣ መብረቅና ከባድ ዝናብ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።