11-20 September 2026
በመጪዎቹ የሴፕቴምበር ሁለተኛው አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይሄዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው አህዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ። ስለሆነም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡