11-20 September 2025

Bulletin

በመጪዎቹ የሴፕቴምበር ሁለተኛው አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በፀኃይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡