11-20 October 2026

Bulletin

በመጪዎቹ የኦክቶበር ሁለተኛዉ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም ከተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መከከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡