በሚቀጥሉት የኦክቶበር ሁለተኛዉ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም የተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የምስራቅ ቦረና፣ የምዕራብ ጉጂ፣ ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡