11-20 November 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት ቀናቶች ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተለይም በመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናቶች ላይ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አከባቢዎች ላይ ይልበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጉጂ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ በመጠንም እና በስርጭት የተሻለ ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም በፀሀይ ሀይል ታግዘው ከሚጠናከሩት የደመና ክምችቶች ላይ በመነሳት በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ11 እስከ 30 ሚ.ሜ የሚደርስ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡