11-20 November 2025

Bulletin

በሚቀጥሉት የኖቬምበር የሁለተኛዉ አሥር ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በተለይም ከሳምንቱ አጋማሽ በኋላ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት የሰሜን፣ መካከለኛዉ፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ አዊ፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሺ እና የማኦኮሞ ልዩ ዞን፤ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም በሚኖሩት ደረቅ ቀናቶች የደረሱ ሰብሎች መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡