በሜይ የሁለተኛዉ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በመሆኑም በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀጣይነት እንደሚኖራቸውና በተለይም የምድር ወገብን በማቋረጥ ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተሻለ የደመናና ሽፋንና የዝናብ ሥርጭት ይኖራቸዋል፡፡