11-20 May 2025

Bulletin
Document

በሜይ የሁለተኛዉ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ  እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ (ካርታ 1)። በመሆኑም በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም ከሳምንቱ አጋማሽ በኃላ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸውና በተለይም የምድር ወገብን በማቋረጥ ወደ ሀገራችን የሚገባው ዕርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተሻለ የዝናብ ሥርጭት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፤ በደቡብ ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት  ይኖራቸዋል::