11-20 March 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ፣ የስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች፣ የመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ላይ የተሻለ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በደቡብ፣ መካከለኛዉ፣ ምስራቅና እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡