
በጁን የሁለተኛዉ አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይሄዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም፤ በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ስለሆነም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብና በመካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡