
በጁላይ ሁለተኛ አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይሄዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስለሆነም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡