11-20 January 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት የጃንዋሪ አስር ቀናት በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በመጀመሪያዎቸ ስድስት ቀናት ላይ በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መከከለኛዉና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የለሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት (5) ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ