በፌብርዋሪ የሁለተኛዉ አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በስምጥ ሸለቆ እና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ መካከለኛውና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ከሳምንቱ አጋማሽ በኋላ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ የስምጥ ሸለቆ እና አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡