በሚቀጥሉት የዲሴምበር ሁለተኛዉ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጥቂት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናቶች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ ሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በመሆኑም በደቡብ ኦሮሚያ የሚገኙ የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ እንዲሁም የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ላይ የሚገኘዉን አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአግባቡ በመሰብሰብ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ ያስፈልጋል፡፡