11-20 April 2025

Bulletin
Document

በመጪዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ይበልጥ እየተጠናከሩና እየተስፋፉ እንደሚሄዱ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፤ በመካከለኛዉ፣ በምስራቅ፣ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በበልግ አብቃይ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ፡፡በተጨማሪም በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብና በመካከለኛዉ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡