1-10_March 2025

Bulletin

ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በበልግ አብቃይ አከባቢዎች በሆኑት የመካከለኛዉ፣ የሰሜን ምስራቅ፣ የደቡብ ምዕራብ እና የደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸው የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ፤ በመካከለኛዉ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡