1-10_June 2024

Bulletin

በሚቀጥለው አሥራ ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ