
በመጪዎቹ የሴፕቴምበር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ በተለይም በምዕራብ አጋማሽ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካካለኛው፣ እንዲሁም በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ፡፡