1-10 October 2026

Bulletin

በመጪዎቹ የኦክቶበር የመጀመሪያዋቹ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም ከተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከዕለት ወደ ዕለት የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፣ እና ላይ ከቀላል እስከ መከከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡