
በመጪዎቹ የኦክቶበር የመጀመሪያዉ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም ከተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ