1-10 November 2026

Bulletin

በሚቀጥሉት የኖቬምበር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም የተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተለይም በመጨረሻዎቹ ቀናቶች ላይ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጉጂ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡