1-10 November 2025

Bulletin

በሚቀጥሉት የኖቬምበር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት አሁን ከሚታዩትና በቀጣይነትም የተተነበዩት የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡