
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማለ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፤ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል (ካርታ 7)፡፡ በመሆኑም በበለግ አብቃይ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ (ካርታ 7)፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ፤ በመካከለኛዉ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ (ካርታ 7 )፡፡