በሚቀጥሉት የጃንዋሪ የመጀመሪያው አሥር ቀን ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ኦሮሚያ፤ ሲዳማ ክልል፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በመሆኑም በደቡብ ኦሮሚያ የሚገኙ የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ እንዲሁም የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ላይ የሚገኘዉን አነስተኛ መጥን ያለዉ ዝናብ በአግባቡ በመሰብሰብ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ ያስፈልጋል ፡፡