1-10 February 2024

Bulletin

በጃንዋሪ ወር የመጨረሻዎቹ ቀናቶች አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደረቅ፣ ፀሐያማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥቂት ቀናቶች የስምጥ ሸለቆና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች፤ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች ላይ ከነበረው የደመባ ሽፋን በመነሳት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የነበራቸው ሲሆን፤ በጥቂት አካባቢዎችም ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡