በሚቀጥሉት የዲሴምበር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጥቂት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናቶች ላይ በተዳከመ ሁኔታ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ በመሆኑም በደቡብ ኦሮሚያ የሚገኙ የቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ እንዲሁም የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ላይ የሚገኘዉን አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአግባቡ በመሰብሰብ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ ያስፈልጋል ፡፡