Seasonal Climate Bulletin Bega 2024-25

Bulletin

በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጉጂ፤ በቦረና፤ በሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች መደበኛ የዝናብ ሁኔታ፤ እንዲሁም የሶማለ ክልል ደቡባዊ ክፍል ከመደበኛ በታች ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሰሜን፤ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡