Kiremt 2026 Seasonal Climate Forecast

Bulletin

በክረምት 2018/19 ዓ.ም፡-

በደቡብና ምስራቅ ትግራይ፤ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የአፋር ክልል ዞኖች እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በታች (ካርታ 4)፡፡

የመካከለኛውና ምዕራብ ትግራይ ዞኖች እና ምዕራብ አማራ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻው ላይ መደበኛና በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከመደበኛ በታች፤

የቤንሻንጉልጉሙዝ ክልል ዞኖች፤ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ የጋምቤላ ክልል ዞኖች እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ፤

በተጨማሪም የመካከለኛውና የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በታች ዝናብ ያገኛሉ፡፡

የክረምት የዝናብ አጀማመርም በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ቀድሞ የሚጀምር ሲሆንና፤ በአብዛኛው አከባቢዎች ላይ ደግሞ መደበኛ ፈሩን ተከትሎ ይጀምራል፡

በክረምት ወቅት ተከታታይነት ያላቸው የዝናብ ቀናት የሚኖሩ ሲሆን፤ አልፎ አልፎም ተከታታይነት ያለው ደረቅ ቀናቶች እንደሚኖሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የክረምቱ አወጣጥም በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚዘገይ ሲሆን፤ ከሰሜን ምስራቅና መካከለኛው አከባቢዎች ላይ ቀደም ብሎ ሊወጣ እንደሚችል አሁን ላይ ያሉት የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡