Kiremt 2025 National Climate Forecast

Bulletin

በሚቀጥለው የክረምት ወቅት የሚጠበቀውን የአየር ጠባይ ትንበያን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና የሚገኘውን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ በመጠቀም በግብርናው እንቅስቃሴ፣ በዉሃ ሃብት አስተዳደር እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎችን ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር ማከናወን ያስፈልጋል፡፡ የወቅቱ ዝናብ አጀማመር በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ቀድሞ የሚጀምር ሲሆንና፤ በአብዛኛው አካባቢዎች ላይ ደግሞ መደበኛ ፈሩን ተከትሎ ይጀምራል፡፡ በተጨማሪም በክረምት ወቅት ተከታታይነት ያላቸው የዝናብ ቀናት ይኖራሉ፡፡ የክረምቱ አወጣጥም በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚዘገይ ሲሆን ከአብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች ላይ ደግሞ መደበኛ ፈሩን ተከትሎ እንደሚወጣ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡