በመሆኑም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል መደበኛ፤የቦረናና ጉጂ ዞኖች፤የሲዳማ፤ የማዕከላዊና የደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛና ከመደበኛ በላይ፤በሌላ በኩል የደቡብ ትግራይ፤ የምስራቅ አማራ፤ አፋር፤ መካከለኛው እና የምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖር ትንበያ ተሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡በተጨማሪም የምዕራብ አማራና የጥቂት የቤንሻንጉልጉሙዝ ሰሜናዊ ክፍል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡