Belg 2024 Outlook

Bulletin

በመጪው እ.ኤ.አ 2024 የበልግ ወራት በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት ለደቡብና ለአብዛኛው ለደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡በተመሳሳይም የሰሜን ምስራቅ፣ የመካከለኛውና የሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በተጨማሪም የምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች በአብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ግንዛቤ ተወስዷል። የወቅቱ የዝናብ አጀማመር ቀድሞ እንደሚጀምርና በአወጣጥ ረገድ ግን የሚዘገይ ሲሆን በደቡብ ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከመጪው ክረምት ጋር እንደሚገጣጠም የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡