በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጉጂ፤ በቦረና፤ በሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች ከመደበኛዉ ጋር የተቀራረበየዝናብ ሁኔታ፤ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል ከመደበኛ በታች ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሰሜን፤ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡