February 2024

Bulletin

በጃንዋሪ በመጀመሪያው እና በሁለተኛዉ አስር ቀናቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አልፎ አልፎ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ የዝናብ ስርጭት ነበራቸው፡፡ እንዲሁም በሶስተኛዉ አስራ አንድ ቀናት ከተጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም በበጋ ወቅት ዝናብ የማያገኙትን የሀገሪቱ አካባቢዎችን ጨምሮ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ በአንዳንድ ቦታዎቻቸዉ ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ የተመዘገበበት ወር ነበር፡፡