1-31_May 2024

Bulletin

በመጪው ወር ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩና ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀደሙት ሶስት የበልግ ወራት በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ ዝናብ በብዙ የሀገሪቱ ቦታዎች ላይ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢ ላይ እንደሚኖርና በአንዳንድ ሥፍራዎችም ላይ ከባድ ዝናብ የሚዘወተርና አልፎ አልፎ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።