1-31_ January 2025

Bulletin

በሚቀጥለው የጃንዋሪ ወር በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ጠባይ ይስተዋላል፡፡ በሌላ በኩል ከወሩ አጋማሽ በኋላ ከሚጠናከሩ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ላይ በመነሳት በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በመካከለኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡