
በመጪዉ የኦክቶበር ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ገጽታ እንደሚኖራቸውና በሂደትም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ የሁኑት የደቡብና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጸሀይ ሀይል በመታገዝ ከሚጠናከሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጥቂት የምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራል