
በመጪው ወር ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩና፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከባለፉት የበልግ ወራት በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ ዝናብ በብዙ የሀገሪቱ ቦታዎች ላይ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚኖርና በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ የስምጥ ሸለቆ እና አጎራባች በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ጎርፍ የማስከትል አቅም ሊኖረው ስለሚችል ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ፡፡