1-31 March 2026

Bulletin

በሚቀጥለው የማርች ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ላይ የተሻለ ገጽታ እንደሚኖራቸዉ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በመካከለኛዉ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑተ በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በማርች ወር የወቅቱ ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ከዕለት ወደ ዕለት አንፃራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።