1-31 July 2026
በመጪው የጁላይ ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛዉና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩ ደመናዎች ላይ በመነሳት ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ::