በሚቀጥለው የጃንዋሪ ወር በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ጠባይ እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ከሚጠናከሩ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ላይ በመነሳት በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በመካከለኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡