1-31 December 2025

Bulletin

በመጪው የዲሴምበር ወር በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ቀጣይነት እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መከከለኛዉና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አልፎ አልፎ ሊጠናከር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡