1-31 August 2026
በመጪው የኦገስት ወር ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እየተሻሻሉ ሊሄዱ እንደሚችሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛዉ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በፀሐይ ሀይል ታግዘዉ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በመነሳት አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡